ሁሉንም አካታች የፋሽን ትርዒት

fashion-for-disabled
ሒልተን ሆቴል ተዘጋጅቶ በነበረው አካታች የፋሽን ትርዒት ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸውና የሌለባቸው ሞዴሎች ተሳትፈዋል

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትን የሚወክሉና አፍሪካዊ ዲዛይነሮችንና ሞዴሎችን በአንድ መንደር ያዋለው የሀብ ኦፍ አፍሪካ የፋሽን ሳምንት የተጠናቀቀው ያለፈው ሳምንት ዓርብ ማምሻውን ነበር፡፡ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወ/ሮ ማህሌት ተክለማርያም እንደሚሉት፣ ዝግጅቱ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ነው የተካሄደው፡፡ ዓላማውም የአፍሪካ ዲዛይነሮችን በተለይም የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች ሥራ ለዓለም የሚተዋወቁበትን መድረክ መፍጠር ነው፡፡ ‹‹ዲዛይነር አይደለሁም ግን ፋሽን በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ለዚህ ነው ወደ ማስተዋወቁ የገባሁት፤›› የሚሉት አዘጋጇ የሀብ ኦፍ አፍሪካ ዓመታዊ ፕሮግራም የተቋቋመለትን ተግባር እየተወጣ እንደሚገኝ ያምናሉ፡፡

ከዛሬ ሰባት ዓመታት በፊት አንድ ብለው ሲጀምሩ ስድስት ኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች፣ ስድስት ደግሞ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተገኙ የፋሽን ባለሙያዎች ሥራ የቀረበበት ነበር፡፡ ማፊ፣ ፍቅርተና አይኒ ዲዛይኖች ከጅምሩ አብረዋቸው የነበሩ ዓለም አቀፍ ታዋቂነትን ያተረፉ ኢትዮጵያዊ የፋሽን ብራንዶች ናቸው፡፡ ‹‹አሁንም ብዙ አዳዲስ ዲዛይነሮች ወደ መድረክ እየወጡ ነው፤›› የሚሉት ወ/ሮ ማህሌት፣ በፋሽን ረገድ ተስፋ ሰጪ ጅምሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡ ቀሪውን ያንብቡ >>

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*